Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በትምህርት ዘመኑ ከ7 ሚሊዮን በላይ ደብተር ተሰራጭቷል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 የትምህርት ዘመን ከ7 ሚሊዮን በላይ ደብተር መሰራጨቱን የአዲስ አበባ ከተማ ምገባ ኤጀንሲ አስታወቀ።
 
የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ምነወር ኑረዲን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፤ ከ997 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች 8 ሚሊዮን ደብተር ለማሰራጨት ዕቅድ ተይዟል።
 
ባለፉት 15 ቀናት ውስጥም ከ7 ሚሊዮን በላይ ደብተር ለክፍለ ከተሞች ተከፋፍሎ ለተማሪዎች መሰራጨቱን ተናግረዋል ።
 
ከዚህ በተጨማሪ ከ997 ሺህ በላይ ለሆኑ ተማሪዎች ዩኒፎርም እየተሰራጨ እንደሆነ አመልክተዋል።
 
በአንድ አቅራቢ ድርጅት ምክንያት የዘገየ አንድ ሚሊየን ደብተር ከውጭ ተገዝቶ እንደገባ እንደሆነ ጠቅሰው፤ ደብተሩ እንደደረሰ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለተማሪዎች እንደሚሰራጭ አረጋግጠዋል።
 
የተሰራጨው ደብተር ለተማሪዎች መድረሱን ለማረጋገጥም በቀጣይ ቡድን ተዋቅሮ በየትምህርት ቤቶቹ ክትትል ይደረጋል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ የሚሰራጨው ደብተር እንደየ ተማሪዎቹ የክፍል ደረጃና የሚወስዱት የትምህርት ብዛት ይለያያል ብለዋል።
 
በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ከቅድመ አንደኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች መንግስት የትምህርት ግብዓቶችን በራሱ ወጪ እያቀረበ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።
 
በመሳፍንት እያዩ
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.