በትግራይ ክልል በጤና ስርዓት ማነቆ ላይ ያተኮረ ሪፎርም በአራት ሆስፒታሎች ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ሳይተገበር የቆየው በጤና ስርዓት ማነቆ ላይ ያተኮረ ሪፎርም በአራት ሆስፒታሎች ተጀምሯል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ ሪፎርሙ ግብዓቶች እስከሚሟሉ ድረስ የሚጠብቅ ሳይሆን ያለውን ሀብት እና ፈጠራ በመጠቀም ውጤታማ ስራ መስራት ላይ እንደሚያተኩር ገልጸዋል፡፡
የወደሙ ጤና ተቋማትን መገንባት እና የተጓደሉ የህክምና ግብዓቶችን ከማሟላትን ጎን ለጎን ባለው ሃብት ውጤታማ ሥራ ለመስራት የሪፎርሙ ትግበራ መጀመር አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
ሪፎርሙ በሌሎች ክልሎች ቀደም ብሎ መጀመሩን ያስታወሱት ዶክተር አየለ፥ በትግራይ ክልልም መጀመሩ ባለው ሀብት ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት እንደሚረዳ ጠቁመዋል።
ጤና ሚኒስቴር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ነው የገለፁት።
የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አማኑኤል ሃይሌ በበኩላቸው መሻሻል ያለባቸውን ግብዓቶችና አሰራሮች ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን ነው የተናገሩት።
በክልል ደረጃ ሁሉም የጤና አገልግሎት ሰጭ ሪፎርሙን ተግባራዊ በማድረግ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጥ ትኩረት ይደረጋል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!