Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አፋር ክልል ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆን የልማት ሥራዎችን ለመገምገም እና የበጋ ስንዴ ምርት ሥራን ለማስጀመር አፋር ክልል ገብተዋል፡፡

በዱብቲ ወረዳ ኅብረተሰቡ በ8 ሺህ ሔክታር መሬት ላይ የበጋ ስንዴ ለማምረት ዝግጅት ማድረጉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያላክታል፡፡

በያዝነው ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ በ3 ሚሊየን ሔክታር ላይ የበጋ ስንዴ ለማምረት ዕቅድ መያዙም ተመላክቷል፡፡

በዋናነት በአርብቶ አደርነት የሚታወቀው እና በግብርና ግብዓቶች የቀዳሚ ድጋፍ መዳረሻ ያልሆነው የአፋር ክልል÷ በአሁኑ ወቅት በሀገር አቀፉ የግብርና ምርታማነት ላይ በስንዴ፣ በጥጥ እና በሙዝ ምርት አስተዋፅዖው እጅግ ከፍ እያለ መጥቷል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.