Fana: At a Speed of Life!

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የቀድሞ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ በቀለ ሙለታ ሥርዐተ ቀብር ተፈፀመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የቀድሞ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ በቀለ ሙለታ ሥርዐተ ቀብር ተፈጽሟል።

አቶ በቀለ በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ለበርካታ አመታት በሃላፊነት አገልግለዋል።

በ1963 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የተወለዱት አቶ በቀለ ሙለታ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በወሰን ሰገድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ደግሞ በአዲስ ከተማ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል።

አቶ በቀለ የልጅነት የሥነጽሁፍ ፍቅራቸውን ለማርካታ በልጅነት እድሜያቸውን ከንባብ ጋር የተቆራኙ ሲሆን በሥነፅሁፍ ዘርፍ የተለያዩ ስራዎችን አበርክተዋል፡፡

በበርካታ ሚዲያዎች ለ30 አመታት ያህል ያገለገሉት አቶ በቀለ÷ የጋዜጠኝነት ስራ ሙያውን ጠብቆ እንዲሰራ በማድረግ ረገድ በርካታ አስተዋፅኦ አበርክተዋል።

አቶ በቀለ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ53 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ሥርዐተ ቀብራቸው ዛሬ ቤተሰቦቻቸው፣ የስራ ባልደረቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በሳህሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።

አቶ በቀለ ባለትዳርና የአንድ ወንድና ሶስት ሴት ልጆች አባት ነበሩ።

በትዕግስት ብርሃኔ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.