የህጻናት ካንሰር ሕክምናን በ8 ሳተላይት ክሊኒኮች ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የህጻናት ካንሰር ሕክምናን በአራት ክልሎች በሚገኙ 8 ሳተላይት ክሊኒኮች ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የካንሰር ህክምናን ተደራሽ ለማድረግ የሳተላይት ክሊኒኮችን ማደረጀት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል፡፡
በምክክር መድረኩ የዩኒቨርሲቲዎች ተወካዮች፣ የጤና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት፣ ባለድርሻ አካላት፣ አጋር ድርጅቶች እንዲሁም የክልል ጤና ቢሮዎች ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
የምክክር መድረኩ በፕሮጀክቱ ላይ በተካሄደው የዳሰሳ ጥናት የተገኙ ውጤቶችን ለተሳታፊዎች እና ባለድርሻ አካላት ለማቅረብ ያለመ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ከማይ ቻይልድ ማተር፣ ሳኖፌ እና አስላን ፕሮጀክት አጋር ድርጅቶች በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የህጻናት ካንሰር ህክምናን በአራት ክልሎች በሚገኙ 8 ሳተላይት ክሊኒኮችተደራሽ ለማድረግ መታቀዱ ተገልጿል፡፡
ፕሮጀክቱ ከጥር ወር ጀምሮ ለቀጣይ ሁለት ዓመታት እንደሚተገበርና ጤና ሚኒስቴርም ለፕሮጀክቱ ስኬታማነት ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራ ተጠቁሟል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!