የጨጓራ ሕመም እንዳይባባስ መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የበርካቶች የጤና ዕክል የሆነው የጨጓራ ሕመም ጥንቃቄ በጎደለው አመጋገብ፣ መጠጥ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች እንደሚባባስ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
ሕመሙ እንዳይባባስም ለጨጓራ ቱቦ አለመዘጋት ችግር በአመጋገብ እና መጠጥ ላይ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ነው ባለሙያዎች የሚመክሩት፡፡
ለምሣሌ ካፊን (አነቃቂ ነገር) ያላቸው መጠጦችን አለመጠቀም፣ ቅባትነት ያላቸው ምግቦችን አለመመገብ፣ አሲድ ያላቸው ምግቦችን አለመመገብ፣ አልኮል ያላቸው እና ለስላሳ መጠጦችን አለመጠቀም ይመከራል፡፡
እንዲሁም ለጨጓራ ቱቦ አለመዘጋት ችግር ከሚመከሩ ጥንቃቄዎች መካከል÷ በልቶ አለመተኛት (ቢያንስ ለሦስት ሠዓት)፣ ትራስ መጠቀም እና በአንድ ጊዜ ብዙ አለመመገብ የሚሉት ይገኙበታል፡፡
ምንጭ፡- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ