Fana: At a Speed of Life!

መከላከያን መደገፍ የሃገር ህልውናን ማስጠበቅ የሃገር ሉአላዊነትን መደገፍ ነው- አብርሃም በላይ(ዶ/ር)

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መከላከያን መደገፍ የሃገር ህልውናን ማስጠበቅ የሃገር ሉአላዊነትን መደገፍ ነው ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትሩ አብርሃም በላይ(ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷መከላከያ ሃገር ነው፤ መከላከያን መደገፍ የሃገር ህልውናን ማስጠበቅ፣ የሃገር ሉአላዊነትን መደገፍ ነው ብለዋል ::

መከላከያ ሲነካ፣ መከላከያ ሲደፈር ሃገር ተደፈረች! የምንለውም ለዚህ ነው ያሉት አብርሃም በላይ(ዶ/ር) የሃገር መከላከያ ሰራዊት ብሔሩም፣ ዘሩም፣ ሃይማኖቱም ሆነ እምነቱ፥ ኢትዮጵያ እና ህዝቦችዋ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል::

ስለሆነም በአሁኑ ጊዜ ከዘር፣ ከመንደርና ከጎጥ የአስተሳሰብ ወጀብ ሳይበግራቸው፣ ሃገርና ህዝባቸውን አስቀድመው ፣በአቋማቸው ፀንተው በመታገል ዓርአያ ለሆኑ ጀግኖች መከላከያ ዕውቅና ሰጥቷል ብለዋል::

ይህ ዕውቅና አገር የሰጠችው እውቅና መሆኑን ገልፀው እውቅና ለተሰጣቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

“ረዥም ማሰብና ማየት ብሎም ለአላማ መፅናት ውጤቱ እንዲህ ያለ ላይ መድረስ ነውና ለህዝባችንና ለሀገራችን ልዕልና ሁላችንም እንትጋ” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.