100 ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችን በመደገፍ ከ56 ሺህ በላይ የሥራ ዕድል ለመፍጠር መታቀዱ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሚቀጥሉ ሦስት ዓመታት በኢ-ኮሜርስ ዘርፍ የተሠማሩ 100 ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችን በመደገፍ ከ56 ሺህ በላይ የሥራ ዕድል ለመፍጠር መታቀዱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ኢ-ኮሜርስን መሰረት ባደረገ ንግድ የተሠማሩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ሥራዎቻቸውን በአዲስ አበባ እያስተዋወቁ ነው።
ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችን ከኢንቨስተሮች ጋር ለማገናኘት ታስቦ የተዘጋጀውን የማስተዋወቂያ መርሐ-ግብር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ አይስ አዲስ እና ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን በትብብር አዘጋጅተውታል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴዔታ ይሹሩን ዓለማየሁ (ዶ/ር) እስከ 2027 ዓ.ም 50 ጀማሪ እና 50 በማደግ ላይ ያሉ ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችን በመደገፍ ከ56 ሺህ በላይ የሥራ ዕድል ለመፍጠር መታቀዱን ተናግረዋል።
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ አንዱ ዓላማ÷ ሁሉን አቀፍ፣ ወጣቶች እና ሴቶችን ያማከለ አዳዲስ ሥራዎችን መፍጠር እና የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ነው ብለዋል፡፡
በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የተደገፉ ሥራዎችን በመፍጠር የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ለማፋጠን ይሠራል ማለታቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን የዲጂታል ኢኮኖሚ መሪ አበበ ቸኮል የፋይናንስ አካታችነትን በመፍጠር የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማሣደግ የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፉ አረጋግጠዋል፡፡
የአይስ አዲስ መሥራች እና ሥራ አስፈፃሚ ማርቆስ ለማ በበኩላቸው÷ ለጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ተገቢውን ትኩረት መስጠት ከተቻለ በኢትዮጵያ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል አመላክተዋል፡፡
መንግሥት ለኤሌክትሮኒክስ ንግድ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የኢ-ትራንዛክሽን አዋጅ፣ የብሔራዊ የፋይንሻል ሥትራቴጂ እና የግል ዴታ ጥበቃ አዋጅ የመሳሰሉ የሕግ ማዕቀፎችን አዘጋጅቷል ተብሏል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!