Fana: At a Speed of Life!

ፀፀትን እንዴት ከራስዎ ያርቃሉ?

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰዎች የሚሰማቸው የሃዘን፣ የቁጭት እና የመረበሽ ስሜት ድምር ፀፀት ይባላል፡፡

የሥነ – ልቦና ባለሙያው ሔኖክ ሃ/ማርያም ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ፀፀት ስለሚያመጣው ጉዳትና መወሰድ ስላለባቸው መፍትሄዎች አብራርተዋል፡፡

ፀፀት የተሻለ ስራን ለመስራት ወኔ ቢፈጥርም ከልክ ካለፈ ግን ቀላል የማይባል ተጽዕኖን ይፈጥራል፡፡

በዚህም ይህ ውስብስበ ስሜት ምክንያት ነው ብለው የሚያስቀምጧቸው ነገሮች
– ሥህተት መስራት እና
– እንከን የለሽ ሆኖ ማደግ፡ – በልጅነት ጊዜያቸው ፍጹም በመሆን ተጽዕኖ ውስጥ ያለፉ መሆን
ፀፀት በርካታ ጉዳቶች አሉት፡፡ ከእነዚህም ውስጥ
– የመስራት አቅምን ይነጥቃል
– የበታችነት ስሜት ይፈጥራል
– ተስፋ መቁረጥ
– ኢኮኖሚ ችግር እና
– ማህበራዊ ችግር
ፀፀት የከፍተኛ ጭንቀትና ድባቴ ውስጥ ከሚከቱ የስሜት መዘበራረቆች መካከል አንዱ ሲሆን ፥ ይህ ከተባባሰ የአካልና የአዕምሮ እክልን ያስከትላል ይላሉ ባለሙያው፡፡

ፀፀት ውስጥ እንዳይገቡ መፍትሄው ምንድን ነው
– ስህተትን አምኖ መቀበል
– የሚታረም ከሆነ በቻሉት አቅም ለማረም ጥረት ማድረግ
– አካባቢን መቀየር
– ሥር የሰደደ እና ድጋፍ የሚያስፈልግዎ ከሆነ የህክምና ባለሙያዎችን ድጋፍ ማግኘትና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.