በመዲናዋ የተከናወኑ ተግባራት የነዋሪውን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ጀምረዋል – ከንቲባ አዳነች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለህዝብ የገባነውን ቃል ተግባራዊ ለማድረግ የሰራናቸው ስራዎች የነዋሪውን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እና ማህበራዊ ፍትህ ማንገስ ጀምረዋል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል::
በመድረኩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ÷ የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም የከተማ አስተዳደሩ መዋቅር አካላት ተናብበው እና ተቀናጅተው የሰሯቸው ስራዎች ውጤታማ ሆነው የተጠናቀቁበት እንደሆነ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ለህዝብ የገባነውን ቃል ተግባራዊ ለማድረግ የሰራናቸው ስራዎች የነዋሪውን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እና ማህበራዊ ፍትህ ማንገስ ጀምረዋል ማለታቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡