አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና ኤምባሲ ጋር ስምምነት ፈረመ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱ በተፈረመበት ወቅት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣን ዢዋን ተገኝተዋል።
ስምምነቱ ለ120 ቅድመ እና ድኅረ- ምረቃ ተማሪዎች ነጻ የትምሕርት ዕድል መስጠት የሚያስችል ነው፡፡
ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ከኤምባሲው ጋር ያደረገው ስምምነት የትምሕርት ጥራትን በማሣደግ ብቁ መምኅራንና ተማሪዎችን በማፍራት ረገድ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል፡፡
አምባሳደር ዣን ዢዋን በበኩላቸው÷ ስምምነቱ ዩኒቨርሲቲው በትምሕርት ጥራት በኩል ለሚያከናውነው ሥራ አዲስ ዕድል እንደሚሆን አንስተው፤ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
ዛሬ የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ዓለም አቀፍ ልምድን ወደ ሀገር ውስጥ ለማምጣት ያለመ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ዩኒቨርሲቲው እየፈረማቸው ያሉ መሰል ስምምነቶችም በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንኙነቱን እንዲያሰፋ ያስችለዋል ተብሏል፡፡
በሜሮን ሙሉጌታ