በ2 ነጥብ 3 ሔክታር መሬት ላይ የተገነባው ኮልፌ የግብርና ምርቶች መሸጫ የገበያ ማዕከል ነገ ይመረቃል
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2 ነጥብ 3 ሔክታር መሬት ላይ የተገነባው ኮልፌ የግብርና ምርቶች መሸጫ የገበያ ማዕከል በነገው ዕለት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ይመረቃል::
በከተማው የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋትና አምራችን ከሸማች ጋር በቀጥታ ለማገናኝት ከተማ አስተዳደሩ የግብርና ምርት መሸጫ ማዕከላትን እያስገነባ ይገኛል፡፡
በዚህም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በ2 ነጥብ 3 ሔክታር መሬት ላይ የተገነባውና 4 ህንፃ ያሉት የኮልፌ የግብርና ምርቶች መሸጫ የገበያ ማዕከል ፕሮጀክት ግምባታ ተጠናቆ በነገው ዕለት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡