Fana: At a Speed of Life!

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ምቹና አስተማማኝ የሥራ ዕድል መፍጠር በሚቻልበት አግባብ ላይ ውይይት ተካሄደ

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢንዱስትሪ ፓርኮች ጥራት ያለው፣ ምቹና አስተማማኝ የሥራ ዕድል መፍጠር በሚቻልበት አግባብ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ጋር በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በውይይቸውም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ጥራት ያለው፣ ምቹና አስተማማኝ የሥራ ዕድል መፍጠር፤ የኢንዱስትሪውን ፍላጎት ያማከለ የክህሎት ልማት፣ የሥራ ቦታን ምቹና ሳቢ ማድረግ፣ የሙያ ደህነትና ጤንነት፣ የኢንዱስትሪ የሥራ ባህል እንዲሁም ጤናማ የአሰሪና ሠራተኛ ግንኙነት መፍጠርና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ቀጣይነት ያለው የተናበበ ሥራ መስራት እንደሚገባ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል፡፡

ይህ የትብብር ማዕቀፍ በአንድ በኩል በዘርፉ ርካሽ ሳይሆን ብቁና ተወዳዳሪ የሰለጠነ የሰው ሃይል በማፍራት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችል መሆኑን የስራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።

አያይዘውም ኢንዱስትሪዎች የሚያጋጥማቸውን የሰለጠነ የሰው ሃይል ችግር የሚቀርፍ እና በኢንዱስትሪ ፓርኮች ምቹና አስተማማኝ የሥራ ዕድል መፍጠር የሚያስችል ነው ብለዋል።

ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ለሀገራዊ ግቦች ስኬት የቅንጅት ሥራ አስፈላጊነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በትብብር ለመስራት ላሳዩት ቁርጠኝነትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.