Fana: At a Speed of Life!

አረጋውያን የሰብዓዊነት ድልድይ ሆነው ትውልድ እንዲያሻግሩ ተገቢውን ክብር መስጠት ይገባል – ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አረጋውያን የሰብዓዊነት ድልድይ ሆነው ትውልድ እንዲያሻግሩ ተገቢውን ክብር መስጠትና በውሳኔዎች ማሳተፍ ይገባል ሲሉ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) አስገነዘቡ።
32ኛው ሀገር አቀፍ የአረጋውያን ቀን “አረጋውያንን ማክበር ትውልድ ለማሻገር” በሚል መሪ ሀሳብ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሚዛን አማን ከተማ ዛሬ ተከብሯል።
ሚኒስትሯ በበዓሉ ላይ እንደገለጹት አረጋውያን በልምድ የካበተ እምቅ ዕውቀትና ክህሎት እንዳላቸው እና ሀገራዊ ሀብቶች የአረጋውያን አሻራ ያረፈባቸው መሆናቸውን ጠቁመዋል።
አረጋውያን የሰብዓዊነት ድልድይ ሆነው ትውልድ እንዲያሻግሩ ተገቢውን ክብር መስጠትና በውሳኔ አሰጣጥ ላይ ማሳተፍ ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል።
አረጋውያን በጊዜ ሂደት እየተሸረሸረ የመጣውን የመተሳሰብና የአብሮነት ባህል መልሶ የማጎልበት ከፍተኛ አቅም እንዳላቸውም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።
“አረጋውያን ትናንት ሀገር ለገጠማት ፈተና ሳይበገሩና ለነፃነት ታግለው ለዛሬ ያበቁን የጀግንነት ምልክቶች በመሆናቸው ክብራቸውን የሚመጥን ሥራ ሰርተን ልናልፍ ይገባል” ብለዋል።
ሚኒስቴሩ አረጋውያን ያላቸውን እምቅ አቅም ለሀገር ጥቅም እንዲያውሉ ለማስቻል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።
“የአረጋውያን ቀን የአባቶቻችንን መልካም ነገር ከመዘከር ባለፈ አደራ የምንረከብበትና የዜግነት ክብርን ከፍ የምናደርግበት ነው” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.