የቼክ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ ገቡ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ ለገቡት የቼክ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ፒተር ፊያላ አቀባበል አደረጉላቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ፒተር ፊያላ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀጣይ ሁለት ቀና በኢትዮጵያ እንደሚቆዩም ታውቋል።
በቆይታቸውም ከኢትዮጵያ ጋር ባላቸው ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ዙሪያ እንደሚመክሩ የሚጠበቅ ሲሆን የትምህርት፣ ባህልና ማዕድን ዘርፍም ትኩረት ይደረግባቸዋል ተብሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ፒተር ፊያላ ከኢትዮጵያ ቆይታቸው በኋላ በኬኒያ፣ ጋና፣ ናይጄሪያ እና ኮትዲቯር ጉብኝት እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።