ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከቼክ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የቼክ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔትር ፊያላ በጋራ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል::
ለጋራ ልማት እንዲበጀን በሀገሮቻችን መካከል በቆየው ግንኙነት ላይ ተመስርተን ግንኙነታችንን የበለጠ ማጎልበትን ዓላማ አድርገናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ፒተር ፊያላ ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ትናንት ምሽት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ፒተር ፊያላ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል እንዳደረጉላቸው ይታወቃል፡፡