Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ዞን ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የተከናወነው ሥራ ተገመገመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እና የልማት ሥራዎችን ለማጠናከር የተከናወነው ሥራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተገምግሟል፡፡

በክልሉ የተገኘውን ሰላም ለማፅናት ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ፈጠራና የሕዝብ ግንኙነት ሥራ መሠራት እንዳለበት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን በግምገማው ላይ ተናግረዋል፡፡

አሁን የተገኘውን ሰላም አጽንቶ ለማስቀጠል በሚያስችል ደረጃ አመራሩ የጸጥታ ሥራውን ማጠናከር እንደሚገባውም ነው ያሳሰቡት፡፡

የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በመተከል ዞን ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እና የልማት ሥራዎችን ለማጠናከር ያከናወኗቸው ተግባራትና የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ የቀረበው ሪፖርትም÷ በዞኑ የተገኘውን ሰላም ተከትሎ ሕብረተሰቡ ፊቱን ወደ ልማት ማዞሩን እና በመደበኛ ሥራዎች ላይም መነቃቃት መፈጠሩን አመላክቷል፡፡

በተለይ በመኸር እርሻ የተከናወኑ ሥራዎች አበረታች መሆናቸው እና የግብርና ልማት ሥራዎች ላይ የታየው ተነሳሽነት አበረታች መሆኑ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

ሕብረተሰቡን በማሳተፍ የትምህርት ቤት እድሳትና ጥገና ሥራዎች መከናወናቸው የተገለጸ ሲሆን÷ በቀጣይም የመማር ማስተማሩን ሥራ በሚፈለገው ልክ እንዲሄድ ያልተቋረጠ ሥራ ይጠበቃል መባሉን የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የሰላም ተመላሾችን በዘላቂነት የማቋቋምና ተከስቶ በነበረው ግጭት የተጎዱ ተቋማትን የመልሶ መገንባት ሥራን በተጠናከረ ሁኔታ ማስቀጠል እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.