Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የሚገኙ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ዛሬ ይፋ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

ውጤቱ÷ ዛሬ ከምሽቱ 3 ሠዓት ጀምሮ ይፋ መደረጉን ነው አገልግሎቱ ያስታወቀው፡፡

ተፈታኞችም eaes.et ላይ በመግባት የፈተና አዳራሽ መግቢያ መታወቂያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስም ብቻ በማስገባት ውጤታቸውን መመልከት ይችላሉ ነው የተባለው፡፡

እንዲሁም ተፈታኞች በውጤታቸው ላይ ቅሬታ ካላቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ ከላይ በተገለጸው ድረ ገጽ ላይ እስከ ጥቅምት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 ድረስ ማቅረብ እንደሚችሉ ነው የተገለጸው፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.