Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 1 ነጥብ1 ቢሊየን ብር ለመልሶ ግንባታ መደበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኃይል መቆራረጥ ለመቅረፍ 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ለመልሶ ግንባታ መመደቡን አስታወቀ።

የአገልግሎቱ የኮሙኒኬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ ገብሬ ከፋና ብሮድካስቲንግ ጋር ባደረጉት ቆይታ በመዲናዋ የኃይል መቆራረጥ ችግርን ለመቅረፍ እየተከነወነ ስለሚገኘው ስራ አንስተዋል፡፡

በዚህም ፥ ለመብራት መቆራረጥ መንስዔው ለረጅም ጊዜ እድሳትና ማሻሻያ ያልተደረገላቸው የኤሌክትሪክ መሰረት ልማቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።

በመሆኑም የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ለማሻሻል 122 ኪሎ ሜትር የዝቅተኛ መስመር ማሻሻያ፣ 44 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር ማሻሻያ፣ 216 የትራንስፎርመር አቅም ማሻሻያ እንደሚካሄድም ነው የተናገሩት።

በዚህ ዓመት ከአዲስ አበባ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባሉ ከተሞች የተጀመረው መስመር የማደስ ፕሮጀክት ተፈፃሚ ሲሆን መቆራረጡ እንደሚቀንስም ጠቅሰዋል፡፡

በሲሳይ ዱላ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.