ለፓኪስታን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ትልቅ እድል አለ – አምባሳደር ሚያን አቲፍ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓኪስታን አምባሳደር ሚያን አቲፍ ለሀገራቸው ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ትልቅ እድል እንዳለ ተናገሩ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር ሚያን አቲፍ ሸሪፍን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው የሁለቱን ሀገራት የቆየ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ በማድረስ ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል።
አምባሳደር ምስጋኑ በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ አቪዬሽን እና ባህላዊ እና ቴክኒካል ድጋፍ ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ አብራርተው ፓኪስታን ኢንቨስትመንቷን እንድታሳድግ ጠይቀዋል።
አምባሳደር ሚያን አቲፍ በበኩላቸው፥ በኢትዮጵያ እና በፓኪስታን መካከል ያለውን ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት ገልፀዋል፡፡
የፓኪስታን መንግስት በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን መድረኮች ያለውን ግንኙነት የማሳደግ ፍላጎት እንዳለው መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አምባሳደር ሚያን በመቀጠል ኢትዮጵያ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በፋርማሲዩቲካል እና በኮንስትራክሽን ዘርፍ ያላትን ከፍተኛ የኢንቨስትመንት አቅም አድንቀው፤ ይህም ለፓኪስታን ባለሃብቶች ትልቅ እድል እንደሆነ ጠቁመዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!