Fana: At a Speed of Life!

መሠረተ ልማቶች የሚጠበቀውን የጥራት ደረጃ እንዲያሟሉ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመላው ሀገሪቱ የሚገነቡ መሠረተ ልማቶች የሚጠበቀውን የጥራት ደረጃ ያሟሉ እንዲሆኑ እየተሠራ መሆኑን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ገለጸ።
 
ጥራትን በጠበቀ የመሠረተ-ልማት ኢንቨስትመንት አተገባባር ዙሪያ ሀገር አቀፍ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው።
 
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ጥራት ያለው መሠረተ ልማት ለዘላቂ የከተማ ልማት፣ ለኢኮኖሚ ዕድገት እና ለዘላቂ አካባቢ ጥበቃ መሰረት ነው ብለዋል።
 
ይሁን እንጂ ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ታዳጊ ሀገራት ጥራት ያለው መሠረተ ልማትን በማቅረብ ረገድ ፈተናዎች እንደሚገጥማቸው ገልጸዋል።
 
የመሠረተ ልማት የጥራት ችግር የዘርፉ ተግዳሮት ነው ያሉት ሚኒስትሯ በዋናነትም በተለያዩ ባለድርሻ አካላት መካከል ውህደት እና ቅንጅት አለመኖር እና ዝቅተኛ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ችግሮች ተጠቃሽ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
 
መደበኛ እና ወቅታዊ ጥገና አለመኖር፣ የተቋራጮች እና አማካሪዎች የሙያ አቅም ውስንነት፣ በተግባር ላይ የተመሰረተ ትምህርት እና ስልጠና አለመኖር፣ የግንባታ ዕቃዎች እጥረት እና የዋጋ ጭማሪ ፣ የግንባታ ምዝገባ ስርዓት እጥረት እና የግንባታ ፕሮጀክት አስተዳደር ደካማ መሆን ለጥራት ጉድለት አስተዋፅኦው የጎላ መሆኑንም ነው የገለጹት።
 
በመሆኑም መንግስት የመሠረተ ልማት ዝርጋታና ግንባታ የኢኮኖሚ ዕድገት ቁልፍ ሚና የሚጫወት ዘርፍ እንደመሆኑ የመሠረተ ልማትን ጥራት ለማሻሻል በርካታ ውጥኖች ላይ እየሰራ ነው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.