ሳፋሪኮም በግማሽ ዓመት 34 ነጥብ 2 ቢሊየን የኬኒያ ሽልንግ የተጣራ ትርፍ አገኘ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሳፋሪኮም በግማሽ ዓመት 34 ነጥብ 2 ቢሊየን የኬኒያ ሽልንግ የተጣራ ትርፍ ማኝኘቱን አስታወቀ፡፡
የኬንያው ኩባንያ ጠንካራ ሆኖ እንደቀጠለ የገለጸ ሲሆን፥ በግማሽ ዓመቱ የ10 ነጥብ 9 በመቶ የገቢ እድገት በማስመዝገብ በአጠቃላይ 41 ነጥብ 6 ቢሊየን የኬኒያ ሽልንግ ገቢ ማግኘት መቻሉን አስታውቋል።
የአገልግሎት ገቢው 9 ነጥብ 3 በመቶ ያደገ ሲሆን፥ ይህም ወደ 158 ነጥብ 3 ቢሊየን የኬኒያ ሽልንግ አድጓል ማለት እንደሆነ ገልጾ፥ ይህም በዋነኛነት ኤም-ፔሳ እና ሌሎች አገልግሎቶች ተጠቃሽ እንደሆኑም ነው የተነሳው፡፡
የገቢው እድገት ከኩባንያው ኤም-ፔሳ የፋይናንስ አገልግሎት ንግድ በተገኘ ገቢ ነው የተባለ ሲሆን፥ የኢንተርኔት ግንኙነት አቅርቦት ንግዱ እድገት ማሳየቱን የኬንያው ኔሽን ዘግቧል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!