Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በኢራን እንደሚደገፉ በሚነገርላቸው ሶሪያ ውስጥ የሚገኙ ሚሊሻዎች የጦር መሳሪያ መጋዝን ጥቃት ፈፀመች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በኢራን እንደሚደገፉ በሚነገርላቸው ሶሪያ ውስጥ የሚገኙ ታጣቂ ሚሊሻዎች የጦር መሳሪያ መጋዝን ላይ የአየር ጥቃት መፈፀሟን አስታውቃለች፡፡

ጥቃቱ ባለፈው ሳምንት የኢራን ሚሊሻዎች ኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ ለፈፀሙት ጥቃት ምላሽ ስለመሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

ትናንት ምሽት በተፈፀመው ጥቃት የአሜሪካ ኤፍ 15 ተዋጊ ጄቶች በሶሪያ ዴር ኤል ዙር በተባለው ስፍራ በሚገኘው የኢራን አብዮታዊ ዘብ ይዞታ በሆነው የጦር መሳሪያ ማከማቻ ስፍራ በርካታ ቦምብ በመጣል ማውደማቸው ተገልጿል፡፡

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን በሰጡት መግለጫ÷ ዩናይትድ ስቴትስ ራሷን፣ ህዝቦቿን እና ጥቅሟን ለማስከበር ማንኛውንም እርምጃ ትወስዳለች ብለዋል፡፡

ወታደራዊ ምንጮችን ጠቅሶ አሶሺየትድ ፕሬስ እንደዘገበው፤ በወታደራዊ መጋዝኑ ውስጥ ሰላማዊ ሰዎች ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ጠቅሶ በተፈፀው ጥቃትም ንፁሃን ሰዎች መገደላቸውን አስነብቧል፡፡

ይሁን እንጂ የአሜሪካ ባስልጣናት በጥቃቱ ሰላማዊ ሰዎች አልተገደሉም ያሉ ሲሆን በወታደራዊ መጋዝኑ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት የኢራን አብዮታዊ ዘብ አባላት ናቸው ማለታቸውን ዘገባው ጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.