Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ቻይና በትምህርት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከቻይና የትምህርት ሚኒስትር ሁዋይ ጂንፔንግ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ÷ በኢትዮጵያና ቻይና መካከል ባለው የሁለትዮሽ የትምህርት ትብብር ላይ በስፋት መክረዋል፡፡

ሀገራቱ በትምህረት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር አጠናክረው ለመቀጠል መስማማታቸውንም በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

ውይይቱ በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ እየተካሄደ ከሚገኘው 42ኛው የተመድ የትምህርት፣የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) አጠቃላይ ጉባዔ ጎን ለጎን ነው የተደረገው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.