Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዋጋ ግሽበትንና የኢኮኖሚ ጉዳዮችን በሚመለከት ለምክር ቤት አባላት ከሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-

👉ኢትዮጵያ ውስጥ የኑሮ ውድነት አለ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎች በኑሮ ውድነት ምክንያት ለመመገብ ይቸገራሉ ይሄ ጥያቄ እውነት ነው፡፡

👉ኢትዮጵያ ውስጥ ሳይሆን እዚሁ ከእኛ ቢሮ በመቶ ሜትር ርቀት ሰዎች ይቸገራሉ፤ ባለፉት 40 አመታት ያልታየ የዋጋ ግሽበት በዓለም ላይ አለ፤ የኢትዮጵያ ችግር ብቻ ሳይሆን የዓለም ችግር ነው፡፡

👉የኢትዮጵያን ያባባሰው የዋጋ ግሽበቱ የገቢ አቅማችን ዝቅተኛ በሆነበት ሁኔታና ላለፉት በርካታ አመታት ሳይቋረጥ እያደገ ስለመጣ የሰው ገቢና የግሽበት እድገት ምጣኔ በከፍተኛ ደረጃ ኑሮ ላይ ጫና አምጥቷል፡፡

👉ዋናው ችግራችንና ልንሰራበት የሚገባው ጉዳይ ግሽበት ነው ብለን ነበር፤ አንዳንድ ጊዜ ግሽበትንና የኑሮ ውድነትን አንድ አድርገን እናያለን፤

👉የኑሮ ውድነት የሚፈጠረው በዋጋ ግሽበት አደለም፤ ግሽበት እያለ ኑሮ ውድ ላይሆን ይችላል፤

👉የእኛ ችግር የሆነው ገቢያችን እያደገ ስለማይሄድ ነው፡፡

👉ዘንድሮ ያለው ሁኔታ ግን አጠቃላይ የዓለም የዋጋ ሁኔታ መረጋጋት እያሳየ እንደሚቀጥል ይተነበያል፤

👉በፋይናንስ ተቋማት የሚተነበየው ይረጋጋል የሚል ነው፤ የእኛንም ብትወስዱ አምና ስንነጋገር 37 በመቶ ነበር፤ በዚህ አመት መስከረም ላይ 28 በመቶ ወርዷል፤

👉ይህንን ጉዳይ ያወሳሰበው ነገር የእኛ የተደመረ ችግር ብቻ ሳይሆን ያደጉ ሀገራት የወሰዱት እርምጃ ጭምር ነው፤

👉ፈተናን አናስቀረውም፤ አንፈልግህምና አትምጣብን አንለውም፤ ነገር ግን ፈተና ስለሚለያይ እንደ አግባቡ ተገንዝቦ መወጣት ብቻ ነው ያለው መፍትሔ፤

👉ለዘመኑ ፈተና ራስን ማዘጋጀት፤ ፈተናውን እያለፍን እያሸነፍን የምንሄድበትን መንገድ መፍጠር ያስፈልጋል፤

👉ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች እንዳይጎዱ ምርታማነት ማሳደግ፤

👉የኢትዮጵያ አርሶ አደር ግብር አይከፍልም፤ ግብር ለማይከፍል አርሶ አደር ድጎሞ የሚሰጥበት ዋናው ምክንያት ምርትና ምርታማነት ካደገ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ሰዎች ኑሮን በተዘዋዋሪ ይደጉማል በሚል እሳቤ ነው፡፡

👉ማዳበሪያ፣ ስኳር፣ ዘይትና ነዳጅ እንደጉማለን፤ የተማሪዎች ምገባና የቤት እድሳትም አለ፤

👉አዲስ አበባ ውስጥ አርሶ አደሩ ምርቱን በቀጥታ መሸጥ እንዲችል የገበያ ማዕከላት እየተገነቡ ይገኛሉ፤

👉አዲስ አበባ ላይ መሰራት የሚያስፈልገው ጉዳይ የቤት ኪራይ ጉዳይ ነው፤

👉የቤት ኪራይ በትክክል ህግ አውጥተን የማንገራው ከሆነ ሰው በየወሩ የቤት ኪራይ እየጨመረ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች ላይ ችግር እያመጣ ነው፡፡ ይሄን ማስተካከል ይኖርብናል፡፡

👉ዘንድሮ የሩዝ ምርት ላይ በክረምቱም በበጋውም በስፋት ተሰርቷል፡፡ 1 ሚሊየን ሄክታር ገደማ ታርሷል።

👉ከ40 ሚሊየን ኩንታል በላይ የሩዝ ምርትም እንጠብቃለን፡

👉የዕዳ ክፍያ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፡፡

👉ቡና አስፈላጊ እና የገቢ ምንጫችንም ስለሆነ በዓለም ገበያ ስርዓት ውስጥም በቀላሉ የተላመድነው ሸቀጥ ስለሆነ እንዲበላሽ መደረግ የለበትም፡፡

👉ፈተናዎች ግን አሉበት፤ በቡና የነበረውን ችግር እያሻሻሉ መሄድ ያስፈልጋል፤

በየሻምበል ምሕረት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.