Fana: At a Speed of Life!

15 ኪሎ ግራም የሚመዝን ግዙፍ ስኳር ድንች መመረቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ኩርሙክ ወረዳ 15 ኪሎ ግራም የሚመዝን ግዙፍ ስኳር ድንች መመረቱ ተገለፀ፡፡

ስኳር ድንቹ በወረዳው ሁሸር ጉማ ቀበሌ  ከአንድ አርሶ  አደር ማሳ ላይ የተመረተ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ስኳር ድንቹ በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረተ ግዙፍ ስኳር ድንች መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በኢትዮጵያ ደረጃ ደግሞ ሁለተኛ መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በኢትዮጵያ እስካሁን ትልቁ ስኳር ድንች 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ሲሆን በጂንካ ከተማ ውስጥ መመረቱ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.