አፈ- ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ከቻይና ብሔራዊ ሕዝብ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ም/ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ የቻይና ብሔራዊ ሕዝብ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበር ሎሳንግ ጊልትሰን ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያዩ፡፡
ውይይቱን የተከታተሉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ነገዎ (ዶ/ር) እንዳሉት÷ የውይይቱ ዓላማ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነው፡፡
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የፓርላማ ለፓርላማ ግንኙነት ማጎልበት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውንም ነው ለኢዜአ የተናገሩት፡፡
በፓርላማዎች መካከል የልምድ ልውውጥ ለማካሄድም ከስምምነት ላይ መደረሱን በመጥቀስም፥ በሀገራቱ መካከል ያለውን ሁለንተናዊ የትብብር ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ እንደሚሠሩ አረጋግጠዋልም ነው ያሉት።
ኢትዮጵያና ቻይና ዘርፈ ብዙ ትብብር ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን የገለጹት ዲማ (ዶ/ር)÷ ቻይና ለኢትዮጵያ ልማትና ዕድገት አስተዋጽኦ እያደረገች እንደምትገኝ ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንትና በመሰረተ ልማት ዘርፍ ቻይና በስፋት እየሠራች መሆኗንም ነው የተናገሩት፡፡
ኢትዮጵያና ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት በፈረንጆቹ 1970 መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!