አምባሳደር ስለሺ በቀለ ከአሜሪካ የቀድሞ ኮንግረስ አባላት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 6 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር ኢ/ር) ከአሜሪካ የቀድሞ ኮንግረስ አባል ኤዶልፈስ ታውን እና ከውጭ ግንኙነት ኮሚቴ አባሉ ግሪጎሪ ሚክስ ጋር ተወያዩ፡፡
አምባሳደሩ በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት÷ ከቀድሞ የኮንግረስ አባላት ጋር በነበራቸው ውይይት በኢትዮ-አሜሪካ እና በአሜሪካ አፍሪካ ግንኙነት ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።
የኢትዮ አሜሪካ የኢንቨስትመንትን፣ የአፍሪካ የእድገትና ዕድል ድንጋጌ (አጎዋ) እና የንግድ ጉዳዮችን በተመለከተ መወያየታቸውን አስታውቀዋል፡፡
አምባሳደሩ አሜሪካ በአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ እድገት ውስጥ እያበረከተች ላለው አስተዋፅዖ እና ለወደፊትም ሚናዋን ለማስቀጠል ላሳየችው ቁርጠኝነት ምስጋና አቅርበዋል፡፡