Fana: At a Speed of Life!

የም/ቤት አባላት ሕብረተሰቡን በማነጋገር የሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ እየሰሩ ነው – አቶ ተስፋዬ በልጅጌ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምክር ቤት አባላት በተወከሉባቸው አካባቢዎች ሕብረተሰቡን በማነጋገር የሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ እየሰሩ መሆኑን በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ ገለጹ።

አቶ ተስፋዬ ÷ የሕዝብ ተወካዮች የመረጣቸው ሕዝብ ጋር በአካል ተገኝተው በማወያየት ስኬቱንም ይሁን ችግሩን ማድመጥ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በዚህም መሠረት የአስፈጻሚውን አካል አሠራር በመፈተሽ ግብረ-መልስም ይሁን የማስተካከያ ሃሳቦችን በማንሳት ግዴታቸውን መወጣት እንዳለባቸው አንስተዋል።

የምክር ቤቱ አባላትም በየምርጫ ክልሎቻቸው ከኅብረተሰቡ ጋር በነበራቸው ውይይት በርካታ ችግሮች መነሳታቸውን ገልፀዋል።

በተለይም የሰላምና ጸጥታ ጉዳይ፣ የኑሮ ውድነት፣ ሥራ አጥነት፣ የመሠረተ-ልማት ጉዳይ፣ የፕሮጀክቶች መጓተት፣ የሙስና ጉዳይና ሌሎችም ችግሮች በስፋት ተነስተዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የምክር ቤት አባላት ወደ ምርጫ ክልላቸው በመሄድ ከመራጩ ሕዝብ ጋር የሚያደርጉት ውይይት ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣትና የማሻሻያ ሥራዎችን ለማከናወን የሚያግዝ መሆኑን ገልፀዋል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ ሎሚ በዶ በበኩላቸው÷ በምክር ቤት አባላት የምርጫ ክልል ውክልና ሥራ እየተሻሻለ መምጣቱን ተናግረዋል።

በዚህም መድረኮችን በመፍጠር፣ ክትትልና ድጋፍ ጭምር በማድረግ ሕብረተሰቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች በሒደት መልስ እንዲያገኙ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በቀጣይም ሕብረተሰቡን ቀርቦ የማናገርና አስፈፃሚውን አካል የመቆጣጠር እንዲሁም የክትትል ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ነው ያሉት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.