ደቡባዊው ዓለም ለደቡብ-ደቡብ የኢኮኖሚ ትብብር መጎልበት ታላቅ አቅም አለው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ህዳር 7 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ደቡባዊው ዓለም ለደቡብ-ደቡብ የኢኮኖሚ ትብብር መጎልበት ታላቅ አቅም እንዳለው እንረዳለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷”ጠ/ሚ ናሬንድራ ሞዲ የ2ኛውን የደቡባዊው ዓለም ድምጽ ጉባዔ መክፈቻ የመሪዎች ውይይት መርሐ ግብር ስላካሄዱ አመሰግናለሁ” ብለዋል።
በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ትብብር የማጠንከርን፣ በአንድ ድምፅ የመናገርንና በዓለም የኢኮኖሚ ጉዳዮች የጎላ ሚና መጫወትን ሃሳብ መካፈላቸውንም አንስተዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ፈጠራ እና የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ አቅሞችን የመጠቀምን አስፈላጊነት ሃሳብ ማካፈላቸውን ጠቁመዋል፡፡
ያሉንን ሰፊ አቅሞች እና የጋራ የልማት ግቦች ስናጤን ደቡባዊው ዓለም ለደቡብ-ደቡብ የኢኮኖሚ ትብብር መጎልበት ታላቅ አቅም እንዳለው እንረዳለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡