በአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ከ100 ሺህ በላይ መጻሕፍት ዲጂታላይዝ መደረጋቸው ተመላከተ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ከ100 ሺህ በላይ መጻሕፍትን ዲጂታላይዝ በማድረግ ሰዎች ካሉበት ሆነው እንዲጠቀሙ ማድረግ መቻሉን የቤተ-መጽሐፍቱ ዋና ዳይሬክተር ውባየሁ ማሞ (ኢ/ር) ገለጹ።
በቤተ-መጽሐፍቱ የሚገኙ ከ400 ሺህ በላይ መጻሕፍቶች አውቶሜትድ መደረጋቸውን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
በዚህም ምክንያት አንባቢያን የሚፈልጉትን መጽሐፍ በፍጥነት በማግኘት መገልገል እንዲችሉ አድርጓል ነው ያሉት፡፡
ከ100 ሺህ በላይ መጻሕፍትን ዲጂታላይዝ በማድረግ ሰዎች ካሉበት ሆነው እንዲጠቀሙ ማድረግ መቻሉንም ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለጹት።
ቤተ-መጽሐፍቱ ባለፉት ሶስት ወራት ከ900 ሺህ ለሚልቁ ተጠቃሚዎች አገለግሎት እንደሰጡ መናገራቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት በአፍሪካ የመጀመሪያው የሰው ሰራሽ አስተውሎት(አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) የተማሪዎች የውድድር ኤክስፖ ማዘጋጀቱ የሚታወስ ነው፡፡