Fana: At a Speed of Life!

የታላቁ ሩጫ ውድድር በሠላም ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ23ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደው ታላቁ የሩጫ ውድድር በሠላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል አስታውቋል።

በሩጫ ውድድሩ በርካታ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገራት ተሳታፊዎች፣ አምባሳደሮች ፣ ተጋባዥ አትሌቶች እንዲሁም 45 ሺህ ዜጎች መሳተፋቸው ተጠቁሟል፡፡

ውድድሩ በሠላም ተጀምሮ በሠላም እንዲጠናቀቅ በፀጥታ ሃይሉ በኩል በቂ ዝግጅት ከመደረጉ ባሻገር በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ለህብረተሰቡ ተገቢው መረጃ እንዲደርስ መደረጉ ተጠቅሷል፡፡

የዘንድሮ ውድድር በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ኃይሉ የውድድሩ ተሣታፊዎችና የከተማው ነዋሪዎች ያበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን የጋራ ግብረ ሃይሉ አስታውቋል፡፡

ለዚህም ግብረ-ሃይሉ ምስጋና አቅርቧል።

በሠላምና ፀጥታ ዙሪያ ማንኛውንም መረጃ ለመስጠትና የፖሊስ አገልግሎትን ለማግኘትም በስልክ ቁጥር 011-5-52-63-03፣ 011-5-52-40-77፣ 0115-52-63-02 ፣ 011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ መስመር 991 እና 987 መጠቀም እንደሚቻል ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.