Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች ከሕዳር 11 እስከ 15 ቀን ሰብል እንዲሰበስቡ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሰብል በደረሰባቸው አካባቢዎች ከ5ኛ ክፍል በላይ የሆኑ ተማሪዎች ከሕዳር 11 እስከ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ሰብል እንዲሰበስቡ መወሰኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ቢሮው ማምሻውን ባወጣው መግለጫ÷አሁን ላይ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የሰብል መሰብሰቢያ ወቅት መሆኑን አንስቷል፡፡

ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የደረሱ ሰብሎችን እንዳያበላሽም ከ5ኛ ክፍል በላይ የሆኑ ተማሪዎች ከሕዳር 11 እስከ 15 ቀን  2016 ዓ.ም ድረስ ወደ ቤተሰቦቻቸው በመመለስ ሰብል እንዲሰበስቡ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

ትምህርት ቤቶችም ተማሪዎች ከሰብል ስብሰባ ሲመለሱ የባከነውን ክፍለ ጊዜ እንዲያካክሱ ማሳሰቢያ መሰጠቱን የክልሉ ኮሙኒኬስሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.