88 ዜጎች ከቤሩት ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት ድጋፍ 88 ዜጎች ከቤሩት ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
በተለያየ ምክንያት የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሊባኖስ ሲኖሩ የነበሩ ዜጎች እንዲመለሱ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዚሁ መሠረት ከዚህ ቀደም 184 ዜጎችን በዛሬው ዕለትም 88 ዜጎችን ማስመለስ መቻሉን ነው በቤሩት የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክተው፡፡