ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የሳይበር አቅም ግንባታ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን ዓለማየሁ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በጋና አክራ እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የሳይበር አቅም ግንባታ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡
ይሽሩን ዓለማየሁ (ዶ/ር) በጉባዔው ባደረጉት ንግግር ÷ዓለም ለተጋረጠባት የሳይበር አደጋ የተቀናጀ ምላሽ ለመስጠትና የማይበገር የሳይበር ምህዳር ለመፍጠርጉባዔው ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል ።
በመድረኩ ኢትዮጵያ በዘርፉ እያደረገች ያለውን ጥረት እና በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 አፈጻጸም የተገኙ ውጤቶችንና ልምዶችን አካፍለዋል፡፡
ጉባዔው ሁሉም ሀገራት መጻኢ የዲጂታል እድላቸውን ለመወሰን በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ ተቀራርበው በመምከር የጋራ አሰራር እንዲያስቀምጡ ለማስቻል ያለመ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡