Fana: At a Speed of Life!

የአክሱም ጽዮን ማርያም ዓመታዊ የንግሥ በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በየዓመቱ ሕዳር 21 በድምቀት የሚከበረው የአክሱም ጽዮን ማርያም ዓመታዊ የንግሥ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው።

በክብረ በዓሉ ላይ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

እንዲሁም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እና የውጭ ሀገራት የተገኙ እንግዶች በበዓሉ ላይ ታድመዋል።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር የአክሱም ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች አስተባባሪ አቶ ኪዱ ተጠምቀ ለኢዜአ እንደተናገሩት÷ በአካባቢው የሰፈነው ሰላም ሰዎች ከተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች መጥተው በዓል ከማክበር ባለፈ ታሪካዊና ባህላዊ የመስኅብ ስፍራዎችን ለጎብኚዎች ክፍት በማድረግ የቱሪዝምን ዘርፍ ለማነቃቃት ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡

በአክሱምና አካባቢው ያሉ ቅርሶች ለጎብኚዎች ክፍት ሆነው እየተጎበኙ መሆናቸውን አስተባባሪው ጠቅሰዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.