ኢትዮጵያ እና እስራኤል የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
አዲስ አበባ፣ ኅዳር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና እስራኤል የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ ከእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው አምባሳደር ምስጋኑ÷ የኢትዮጵያ እና እስራኤልን የረጅም ጊዜ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር መደበኛ የሃሳብ ምክክሮችን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ለወደፊትም ግንኙነታቸን በሚያጠናክር መልኩ የሁለትዮሽ ግንኙነት ግምገማዎችን እና የፖለቲካ ምክክር መድረኮችን ማድረግ አስፈላጊ ነው ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡