Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኮፕ28 ጉባኤ ጎን ለጎን ከኩባው ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 21 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኮፕ28 ጉባኤ ጎን ለጎን ከኩባው ፕሬዚዳንት ሚግዌል ዲያዝ-ካናል ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም የዓለም የአየር ጠባይ ለውጥ ኃላፊነትን፣ የሁለትዮሽ ትብብርን እና የብሔራዊ ልማት ጉዳዮችን የተመለከተ ውይይት ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ከውይይቱ ባለፈም በኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መካነ ርዕይ/ፓቪሊዮን/ ተገናኝተው ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረትና ያላት ቁርጠኝነት የሚያሳየውን አውደርዕይን ጎብኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.