Fana: At a Speed of Life!

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አነሳሽነት በኢትዮጵያ የተሰራው የአረንጓዴ ልማት በልዩነት የሚታይና አስገራሚ ነው – ቶኒ ብሌር

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 21 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አነሳሽነት በኢትዮጵያ የተሰራው የአረንጓዴ ልማት በልዩነት የሚታይና አስገራሚ ነው ሲሉ የቀድሞ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር ገለጹ።
 
የቀድሞ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጋር በኮፕ28 ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረትና ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳየውን አውደ ርዕይን ጎብኝተዋል።
 
አውደ ርዕዩን ከጎበኙ በኋላም አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ እየታየ ያለው ለውጥ ለማሰብ የሚከብድ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
በግብርናው ዘርፍ እያስመዘገበች ካለው ከፍተኛ እመርታ ባሻገር በአረንጓዴ አሻራ ልማትም የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚያስችል ከፍተኛ ስራ ሰርታለች ብለዋል።
 
በዚህም ቀደም ሲል ከውጭ ታስገባቸው የነበሩ እንደ ስንዴ፣ ሩዝ፣ አትክልትና ፍራፍሬ የመሳሰሉ የግብርና ምርቶች ላይ መሰረታዊ ለውጥ በማምጣት እና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ወደ ውጭ መላክ የቻለችበትን ስኬት አስመዝግባለች ነው ያሉት።
 
ቶኒ ብሌር አክለውም ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማት ላይ የሰራችው አመርቂ ስራ በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ በልዩነት የሚታይ መሆኑን ጠቁመዋል።
 
በኮፕ28 ጉባኤ ላይ ይዛ የቀረበችው አውደ ርዕይም በውጭ ያሉ ማህበረሰቦች የኢትዮጵያ መንግስት በአረንጓዴ ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ምን አይነት አስደናቂ ስራ እየሰራ እንደሆነ ያሳያል ብለዋል።
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.