Fana: At a Speed of Life!

በሐውዜን ከተማ አቅራቢያ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ

 

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 21 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ሐውዜን ከተማ አቅራቢያ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

አደጋው ዛሬ ጠዋት 2:45 አከባቢ ከቆራሮ ቀበሌ 22 ሰዎችን ጭኖ ወደ ሐውዜን ከተማ ሲጓዝ የነበረ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሐውዜን ከተማ ወደ መጋብ መስመር ሲጓዝ ከነበረ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ጋር በተለምዶ ቀያሕታይ ተብሎ በሚጠራው ቁልቁለት ላይ በመጋጨታቸው የደረሰ ነው፡፡

በዚህም የ4 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ10 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት፤ በ8 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡

የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን ከሐውዜን ወረዳ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.