Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ምርት አቅርቦት ሰንሰለትን ለማሳጠር እየተሰራ ነው – አቶ ገ/መስቀል ጫላ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ምርት አቅርቦት ሰንሰለትን ለማሳጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ተናገሩ፡፡

በግብርና ምርቶች አቅርቦትና የግብይት ሠንሠለት አስተዳደር ስርዓት ዙርያ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት ተካሄዷል፡፡

በዚህ ወቅት ሚኒስትሩ እንዳሉት ÷ ከአርሶ አደሩ እስከ ሸማቹ ያለውን የግብርና ምርቶች አቅርቦት ሰንሰለት ስርዓትን በማሳጠር በግብይት ሠንሰለቱ የሚገኙ ተዋንያንን ፍትሃዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል በትኩረት እየተሠራ ነው፡፡

በቅድመ ትግበራ መርሐ ግብርም የግብርና ምርት አቅርቦት ሰንሰለቱን በማሳጠር በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ የግብርና ምርቶችን ለህብረተሰቡ ማቅረብ እንደሚጀመር ጠቁመዋል፡፡

በግብርና ምርቶች አቅርቦትና የግብይት አስተዳደር ስርዓት ላይ የተዘጋጀ ሠነድ በመድረኩ ቀርቦ ውይይት መካሄዱም ነው የተገለጸው፡፡

የአቅርቦት ሠንሠለት ስርዓቱን ለማሳጠር የድርጊት መርሐ ግብር ተዘጋጅቶ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.