የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በጅግጅጋ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 18ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በጅግጅጋ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው።
በዓሉ ”ብዝሃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል።
የዛሬው ቀንም የወንድማማችነት ቀን በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተከበረ የሚገኘው።
ቀኑን ምክንያት በማድረግም ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ልምዳቸውን፣ ተሞክሯቸውን፣ ባህላቸውን፣ እሴቶቻቸውን የሚለዋወጡባቸው መርሐ ግብሮች ተዘጋጅተዋል።
የጅግጅጋ ከተማም በዓሉን ለመታደም ለመጡ እንግዶች በተለያዩ ዘርፎች ዝግጅት በማድረግ ቀልጣፋ አገልገሎት እየሰጠች መሆኑን የከተማዋ አስተዳደር አስታውቋል።
በመላኩ ገድፍ