Fana: At a Speed of Life!

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን በማስመልከት የባህል ኤግዚቢሽን ተከፈተ

 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን በማስመልከት የባህል ኤግዚቢሽን ተከፈተ።

በዓሉ ”ብዝሃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ በጅግጅጋ እየተከበረ ነው።

በዛሬው ዕለትም በዓሉን አስመልክቶ ‘ሕዳር 26 የብዝኃነት ቀን’ በሚል የባህል ኤግዚቢሽን ተከፍቷል።

በባህልና ኤግዚቢሽኑ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የራሳቸውን ባህል፣ ማንነት፣ ወግ እና ትውፊት የሚያንጸባርቁ ባህላዊ ቁሶችን አቅርበዋል።

የባህልና ኤግዚቢሽኑ ኢትዮጵያ የብዝሃነት ተምሳሌት መሆኗን ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ማህበረሰብ ለማሳየት ያለመ ነው ተብሏል።

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህልን በማስተዋወቅ የባህል ልውውጥ እና የህዝቦች ትስስርን ማጎልበት፤ እርስ በርስ እንዲተዋወቁ እድል እንደሚፈጥርም ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም ያደገ ትውውቅን በማረጋገጥ መቻቻልን፣ መከባበርንና አብሮነትን ማረጋጥ እንደሚያስችል ተጠቁሟል።

ሕብረ-ብሄራዊነት ላይ የተመሰረተ ሀገራዊ አንድነት ግንባታ ለማጎልበት ሚናው የጎላ መሆኑም ተመላክቷል።

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.