Fana: At a Speed of Life!

በባሕር ዳር ከተማ በሐሰተኛ ማኅተሞች ማስረጃዎችን ሲሰጡ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር ሐሰተኛ ማኅተሞችን በመጠቀም የተለያዩ ማስረጃዎችን ሲሰጡ ነበር የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በከተማ አሥተዳደሩ ግሽ ዓባይ ክፍለ ከተማ 143 ልዩ ልዩ ማኅተሞች እንዲሁም 112 የተለያዩ ግለሰቦች የቀበሌ መታወቂያዎች መያዙም ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም መሸኛ፣ የነዋነት መታወቂያ፣ ያላገባ፣ የተመላሽ ሠራዊት ማስረጃዎች፣ የቀበሌ ቤት ውል፣ ካርታና ፕላን፣ የቤት ማኅበር ማስረጃ፣ የወሳኝ ኩነት፣ የልደት ካርድ የመሳሰሉ ማስረጃዎች መገኘታቸውን በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የ2ኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወካይ ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ያረጋል ተሻለ ተናግረዋል፡፡

ማኅተሞቹ በሁሉም ክፍለ ከተሞችና ቀበሌዎች በተለያዩ አመራሮች እና ባለሙያዎች ስም የታተሙ መሆናቸውንም ነው ለአሚኮ የተናገሩት፡፡

ተጠርጣሪዎችም በፖሊስ ቁጥጥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.