Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ዓመታዊ ምክክር እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ዓመታዊ ምክክር በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲስ አበባ ከሚገኘው የአውሮፓ ህብረት ልዑክና ከህብረቱ አባል ሀገራት አምባሳደሮች ጋር በፈረንጆቹ 2016 በተፈረመው የጋራ ጥቅም ስምምነት መሰረት ነው ውይይቱ እየተካሄደ ያለው።

በየዓመቱ የሚካሄደው የዘርፉ ምክክር ዛሬ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን መሪነት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

ምክክሩ ኢትዮጵያ ከህብረቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻልና የአውሮፓ ህብረትና አባል ሀገራቱ የመልሶ ግንባታ ስራዎችን እንዲደግፉ ለማግባባት ከህብረቱ ጋር የተፈረሙ ስምምነቶችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ዕድሎችን የሚፈጥር ነው ተብሏል።

በተጨማሪም የትጥቅ ማስፈታታት፣ መልሶ ማቋቋም ሂደት እና ግንባታ ስራዎችን ለመደገፍ የሚያስችል እንደሆነም ነው የተመላከተው።

ሌሎች ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችም በውይይቱ ይዳሰሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በታሪኩ ወ/ሰንበት እና አሸናፊ ሽብሩ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.