በምስራቅ ሸዋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የተዘጋውን መንገድ በፍጥነት ለመክፈት ጥረት እየተደረገ ነው ተባለ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሸዋ ዞን በመተሃራ እና በወለንጪቲ መሃል በደረሰ የትራፊክ አደጋ ምክንያት በወደቀ ተሽከርካሪ ቦቴ የተዘጋውን መንገድ በፍጥነት ለመክፈት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ገለጸ።
በአሮሚያ ክልል ፖሊስ የትራፊክ ፖሊስ ደህንነነት እና ቁጥጥር ዋና መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር በላቸው ትኪ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት÷ በዛሬው እለት በምስራቅ ሸዋ ዞን በመስመሩ በደረሰ የትራፊክ አደጋ መንገድ ተዘግቷል።
መንገዱ ላይ ከባድ ተሸከርካሪ በመውደቁ ለተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እንቅፋት መፍጠሩን አመልክተዋል።
በዚህ የተነሳም ከመትሃራ እና ከወለንጭቲ በኩል የሚመጡ አሽከርካሪዎች ለጊዜው እንቅስቃሴያቸውን እንዲያቆሙ እና መስመሩ እስከሚከፈት በትዕግስት እንዲጠባበቁም ጠይቀዋል፡፡
በአደጋው ምክንያትም የአዲስ አበባ ጂቡቲ መስመር ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ዝግ መሆኑን ጠቅሰው፤ በመስመሩ የሚጠቀሙ አሽከርካሪዎች መንገዱ እስኪከፈት ድረስ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቀዋል።
ይሁን እንጂ ባለማወቅ አሸከርካሪዎች ወደ መስመሩ እየመጡ መሆኑን ኮማንደር በላቸው ተናግረዋል።
በሚኪያስ አየለ