በኤካ ኮተቤ ጠቅላላ ሆስፒታል ተቋርጦ የቆየው መደበኛ ሕክምና መሰጠት ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤካ ኮተቤ ጠቅላላ ሆስፒታል ከኮረና ወረርሽኝ ጊዜ አንስቶ አቋርጦት የነበረውን መደበኛ የጤና አገልግሎት ሙሉ በሙሉ መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡
ሆስፒታሉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት በነበረው ሂደት መደበኛ የሕክምና አገልግሎቱን ማቋረጡ ይታወሳል፡፡
በአሁኑ ወቅትም በሙሉ ዐቅሙ ወደ መደበኛ አገልግሎቱ መመለሱን ነው የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ሙሉቀን ተስፋዬ ለኢዜአ የተናገሩት፡፡
ሆስፒታሉ በኢትዮጵያም ሆነ በምሥራቅ አፍሪካ ተመራጭ የጤና ማዕከል ለመሆን የሚያስችላውን ስትራቴጂ መቅረጹንም አስታውቀዋል፡፡
በተለይም በፋርማሲና መድኃኒት አገልግሎት፣ በሕክምና መሣሪያዎችና ተያያዥ ግብዓቶች ሆስፒታሉ ትልቅ ዐቅም መገንባቱን ጠቅሰው፥ በዚህም ፈጣንና ዘመናዊ የሕክምና አገልግሎት ለህሕብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡
በዘንድሮው ዓመትም በሆስፒታሉ በኤሌክትሮኒክስ የተደገፈ የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የመረጃ ሥርዓቱን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚሆንም ጠቁመዋል፡፡
በሆስፒታሉ የሕክምና ጥራትና አስተዳደር ዳይሬክተር ዶክተር ዮናስ ገብረ እግዚአብሔር በበኩላቸው÷ ሆስፒታሉ የእናቶች፣ ጨቅላ ሕጻናትና የሕጻናት፣ የፅኑ ህሙማንን ጨምሮ የውስጥ ደዌና የቀዶ ሕክምና አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።
በመሆኑም ተገልጋዮች ወደ ሆስፒታሉ እየመጡ አስፈላጊውን ሕክምና ማግኘት እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!