Fana: At a Speed of Life!

ሙላቱ ለማ (ፕ/ር) የዓመቱ ምርጥ ፕሮፌሰር በመሆን ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጆርጂያ ሳቫና ግዛት ዩኒቨርሲቲ የሂሳብ መምህር የሆኑት ኢትዮጵያዊው ሙላቱ ለማ (ፕ/ር) የ2023 ምርጥ ፕሮፌሰር በመሆን ተመረጡ።

ሙላቱ ለማ (ፕ/ር) በዘርፍ የተመረጡት በዓለም አቀፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች ማህበር መሆኑን የአሜሪካ ኤምባሲ አስታውቋል።

ማህበሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሙያዊ ስኬት፣ በአካዳሚክ ውጤት፣ በአመራር ችሎታ፣ በመስኩ ረጅም ጊዜ በማገልገል እና ለማህበረሰብ ባደረጉት አስተዋፅዖ በመመርኮዝ ለባለሙያዎች እውቅና እና ክብር ይሰጣል።

በፈረንጆቹ 2023ም ኢትዮጵያዊውን መምህር ሙላቱ ለማ (ፕ/ር) ምርጥ ፕሮፌሰር አድርጎ መርጧቸዋል።

ሙላቱ ለማ (ፕ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሂሳብ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።

በኦሃዮ ከኬንት ግዛት ዩኒቨርሲቲ በሂሳብ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን ፥ ለ28 ዓመታትም በሳቫና ግዛት ዩኒቨርሲቲ ማስተማራቸው ነው የተገለጸው፡፡

በአጠቃላይም ሙላቱ ለማ (ፕ/ር) ከ30 ዓመታት በላይ የሂሳብ ትምህርትን አስተምረዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.