Fana: At a Speed of Life!

የጥርስ ጤና አጠባበቅ

 

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥርስዎን በቀን ሁለት ጊዜ ጠዋትና ማታ በመቦረሽ የጥርስዎን ጤንነት መጠበቅ ይገባል፡፡

ጥርስዎን በትክክለኛው መንገድ መቦረሽ የጥርስ ንፅህና እንዲጠበቁ እንዲሁም መቦርቦር እና ሌሎች የጥርስ ችግሮችን ለማስወገድ ያስችላል።

ጥርስዎን በትክክለኛው መንገድ ሲቦርሹ፣ ጥርሶችዎ ንፁህ ይሆናሉ፣ ይህም ለአፍ ጤንነት አስፈላጊ ነው።

ለመሆኑ ትክክለኛው የጥርስ አቦራረሽ ምን ይመስላል

1.ጥርስ ብሩሽን ከድዳችን መስመር በ45° በመያዝ መፋቅ፣

2. በዝግታ እና በአጭሩ የጥርስ ብሩሽን በጥርሳችን አካባቢ ወደፊት እና ወደኋላ ማንቀሳቀስ

3. ከዚያም ክብ በመስራት፣ ወደላይና ወደታች፣ የጥርሳችንን ውስጥ፣ በማላመጫቻችን በኩል የጥርሳችን ክፍል ሁሉንም ጥርሶች መፋቅ፡፡

4. ጥርሳችንን ፍቀን ከጨረስን በኋላ ባክቴሪያዎችን እና መጥፎ የአፍ ጠረንን ለማስወገድ ምላሳችንን መፋቅ አለብን፡፡

5. በመጨረሻም አፋችንን በመደጋገም በውሃ መጉመጥመጥ መሆናቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከመጠን በላይ ጥርስን መቦረሽ አስፈላጊ አለመሆኑን እና በሀይል መቦረሽ በጥርስዎ እንዲሁም በድድዎ ላይ ጉዳት እንደሚያስከትል የህክምና ባለሙዎች ይመክራሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.