የብራዚል ልዑክ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ይፋዊ ጉብኝት እያደረገ ነው
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብራዚል ልዑካን ቡድን በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ይፋዊ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል፡፡
ልዑኩ በብራዚል የንግድ፤ ኢንቨስትመንት እና ግብርና ዳይሬክተር አምባሳደር አሌክስ ጂያኮሜሊ የሚመራ ነው ተብሏል፡፡
ጉብኝቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እየመሩ መሆኑን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በዚህ ጉብኝትም ከብራዚል የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!